የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች

ጥቅምት 02/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች በኮምቦልቻ እና ደሴ ከተሞች መጠለያ ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች  3.2 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ ቁሳቁስ ለተፈናቀሉ ወኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡

ካፒቴን በህረዲን አብዱ እንደገለጹት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎችን በመወከል በደሴና ኮምቦልቻ መጠለያ ጣቢያ በመገኘት መጎብኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ለተፈናቃዮች ከሰሙት በላይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡

ካፒቴን አህመድ አባድር በበኩላቸው፣ ከአብራሪ ሰራተኞች በተሰበሰበ 3.2 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ ቁሳቁስ እንደ ዱቄት፣ ጤፍ እና ሩዝ የዕለት ደራሽ ምግቦች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር አህመድ የሱፍ አብራሪዎቹ ላበረከቱት ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከኮምቦልቻ ከተማ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች  ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡