የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከርዋንዳ አቻው ጋር ነገ ይጫወታል

የሴቶች ብሔራዊ ቡድን

መስከረም 25/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ከሩዋንዳ አቻው ጋር ነገ 10 ሰዓት ላይ በባህርዳር ስታዲየም ጨዋታ ያካሂዳል።

ብሔራዊ ቡድኑ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ የመጀመርያ ጨዋታ የሩዋንዳ አቻውን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ መንገዱን ያመቻቸ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ቡድኑ መስከረም 29 እና ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም በሜዳው እና ከሜዳው ውጪ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር የምድብ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታውን እንደሚያካሂድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመልክቷል።