የፌዴራል መንግስት ካቢኔ በነገው ዕለት ለምክር ቤት ይቀርባል

መስከረም 25/2014 (ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገው ዕለት ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

ምክር ቤቱ የመንግስት ካቢኔ ሹመት የማፀደቅ ሥራውን ለነገ ያስተላለፈ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

ምክር ቤቱ በውሎው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚቀርቡ የመንግስት ካቢኔ ሹመትን እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።