የኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻ ለግሉ ዘርፍ ለማስተላለፍ ጨረታ እንደሚወጣ ተገለጸ

ኅዳር 7/2015 (ዋልታ) የኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻ ለግሉ ዘርፍ ለማስተላለፍ ከዛሬ ጀምሮ ዓለም አቀፍ ጨረታ እንደሚወጣ ተገለጸ፡፡

ከኢትዮ ኮም እና ሳፋሪ ኮም ባሻገር ለሦስተኛው የቴሌኮም ዘርፍ ፍቃድ ለመስጠት የዓለም አቀፍ የቴሌኮም ድርጅቶች ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ ቀርቧል።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻን ለግሉ ዘርፍ ለማስተላለፍ እና 3ኛ በቴሌ ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ለሚሰማራው ድርጅት ፍቃድ ለመስጠት ጨረታ እንደሚወጣ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ኢትዮጵያ አሁን በስራ ላይ ያሉት የኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም የሚቀላቀለው እና በሦስተኛ ደረጃ ወደ ስራ የሚገባው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ድርጅት በገንዘብ ሚኒስቴር ድረ ገጽ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በሚቆይ ጨረታ ፍላጎታቸውን እንዲያሳውቁ ጠይቀዋል፡፡

በጨረታው አቅም ያለው ተቋም እንደሚመረጥም ተገልጿል።

በቁምነገር አህመድ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW