የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር አከናወኑ

ሐምሌ 22/2014 (ዋልታ) የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሥራ አስፈፃሚዎች እና ሰራተኞች በእንጦጦ ተራራ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርን አከናወኑ።

መረኃ ግብሩን የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አስጀምረዋል።

ተቋሙ ከዚህ ቀደም በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መረኃ ግብር መሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ወደፊትም ይህን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።

በተቋሙ አረንጓዴ አሻራ መረኃ ግብር 800 የሚሆኑ የተቋሙ ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ከ3 ሺሕ በላይ ችግኞችም ተተክለዋል።

በፌናን ንጉሴ