የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሁመድ ጋር ተወያዩ

ታኅሣሥ 5/2014 (ዋልታ) የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሁመድ ጋር ተወያይተዋል።

ዋና ፀሐፊው በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ መጠነኛ አለመረጋጋት ከነበረባቸው ክልሎች አንዱ የነበረውን የሶማሌ ክልል የሰላምና የተስፋ ቀጣና እንዲሆን ላስቻሉት ለሙስጠፌ አመራር አድናቆታቸውን ገልጸው በሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ሊሰሩባቸው በሚችሉ ጉዳዮቸ ላይም መምከራቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።