የእናቶች ጤናን ለማሻሻል እየሠሩ ላሉ አጋር አካላት እውቅና ተሰጠ

የካቲት 24/2014 (ዋልታ) የእናቶች ጤናን ለማሻሻል ከጤና ሚኒስቴር ጋር እየሠሩ ላሉ አጋር አካላት የእውቅና እና የምሥጋና መርኃግብር ተካሂዷል።
በመርኃ ግብሩ ላይ በጤና ሚኒስቴር የእናቶች እና ሕጻናት ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም የጤናማ እናትነት ወርን በተለያዩ የግንዛቤ መስጨበጫ ዝግጅቶች፣ ለእናቶች ጤና ጠቃሚ በሆኑ ተግባራት እንዲሁም በጦርነት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የጤና አገልግሎቱ መነቃቃት መፈጠር የሚያስችሉ ድጋፎች በማቅረብ ሲከበር እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ለዚህ ስኬት ዕውቀታቸውን፣ ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን ላበረከቱ እንዲሁም በእናቶች ጤና ዙሪያ ትልቅ አስተዋፅኦ ለነበራቸው አካላት ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።
በቀጣይም በእናቶች ጤና ዙሪያ ትልቅ ርብርብ እና ጥረት እንደሚያስፈልግ ገልፀው አጋር አካላትም የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል፡፡
በመርኃ ግብሩ ላይ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስክር ወረቀት መሰጠቱን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!