የእንጦጦ የስነ ጥበባት ማእከል ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስጦታነት ተበረከተ

የእንጦጦ የስነ ጥበባት ማእከል

ሐምሌ 18/2013 (ዋልታ) – የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የእንጦጦ የስነ ጥበባት ማእከል ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስጦታነት አበረከተ፡፡

9ሺህ ካሬ ላይ ያረፈው የእንጦጦ የስነ ጥበባት ማእከል ዩኒቨርሲቲው ያለበትን የስነ ጥበብ ማእከል ችግር በዘላቂነት የሚፈታ ከመሆኑም ባሻገር ከያኒያንን ከማህበረሰቡ ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ከመሆን ረገድ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

የአስተሳሰብ ልኬት የሚያሰፋውን ስነ ጥበብ እና የጥበቡን አለም ለማሳደግ ታሳቢ በማድረግ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና መንግስታቸው ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ላበረከቱት የስነጥበብ ማእከል ምስጋና ሊቸረው ይገባል ተብሏል::

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ማእከሉ ለሀገር ዘላቂ ስራ ለመስራት እምነት ተጥሎ እንደተሰጠን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጥበብ ሀብቶችን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳያነት በመጠቀም የጥበቡን አለም ለማሳደግ እንሰራለን ብለዋል::

የዩኒቨርሲቲው ስራ ተግባር ተኮር ላይ ትኩረቱን በማድረግ ለውጤት እንዲሰራም አነሳሽ መሆኑን አክለዋል፡፡

(በሄብሮን ዋልታው)