የኦሮሚያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነዉ

ሐምሌ 23/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የልምድ ልውውጥ ለ11ኛ ዙር “እኔ የንግድ እና የዘርፉ ማህበራት አባል ነኝ” በሚል መሪ ቃል በሱሉልታ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።

በመርኃ ግብሩም የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ታደሰ ገና፣ የአፍሪካ ልህቀት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ምህረት ደበበ (ፒኤችዲ)፣ የሱሉልታ ከተማ  ከንቲባ ሊዲያ ጫሊ አንዲሁም የተለያዩ እንግዶች ተገኝተዋል።

በክልሉ የተጠናከሩ የንግድ ማህበራት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት የተጠናከሩ የንግድ ማህበራትን ለመገንባት የግሉ ዘርፍ አስተዋጽኦ የላቀ እንደሆነ ተናግረዋል።

ህገወጥ ንግድ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለንግድ ማህበራት መጠናከር እንቅፋት መሆናችዉ የተገለፀ ሲሆን የንግድ ማህበረሰቡን ማቀናጀት ችግሮቹን ለመቅረፍ እንደሚያግዝ ተገልጿል።

ከንቲባ ሊዲያ ጫሊ በበኩላቸው በሱሉልታ ከተማ  የንግድ ማህበራትን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገለፀው ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በተለይም ማህበረሰቡን በንግድ ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ተብሏል።

በእመቤት ንጉሴ