የኦሮሚያ ክልላዊ ለሲዳማ ክልል የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

 

በሲዳማ ከልላዊ መንግስት ይፋዊ ምስረታ ክብረ በዓል ላይ

ሀዋሳ፣ የካቲት 15 /2013(ዋልታ) – በሲዳማ ከልላዊ መንግስት ይፋዊ ምስረታ ክብረ በዓል ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ር/መስተዳደር ሽመልሽ አብዲሳ ለክልሉ መንግስትና ነዋሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕት አስተላልፈዋል፡፡

ር/መስተዳደሩ የክልሉ መንግስት ለአዲሱ ክልል የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡

በሲዳማ አጎራባች አካባቢዎች የአፋን ኦሮሞ ትምህርት መስጠት እንደሚጀመርም ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል፡፡

ትስስሩን ይበልጥ ለማጠናከር በመገናኛ ብዙሃን ስርጭት የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ የሲዳማ ቋንቋ፣አፎ ሲዳማ ስርጭት መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡
(በሰሎሞን በየነ)