የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ባሕር ዳር ገቡ

ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

የካቲት 3/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ባሕር ዳር ገብተዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ በባሕር ዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው አሚኮ ዘግቧል።