የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ጋምቤላ ከተማ ገቡ

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

የካቲት 4/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ዛሬ ጋምቤላ ከተማ ገቡ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሚኖራቻው ቆይታ በሁለቱ ክልሎች የሁለትዮሽ የሰላምና የልማት ትብብር ዙሪያ ውይይት እንደሚያደረጉ ይጠበቃል።