የኦሮሚያ ክልል አርቲስቶች ለሰራዊቱ ደም ለገሱ

ነሀሴ 17/2013 (ዋልታ) – የኦሮሚያ ክልል አርቲስቶች እና የኦሮሚያ ባህል ማዕከል ሠራተኞች ለመከላከያ ሠራዊት ደም ለግሰዋል።

የኦሮሚያ  ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ  ከበደ ዴሲሳ ለሀገር ክብርና ሉአላዊነት ሲል በግንባር ለተሰለፈው መከላከያ ሰራዊት ደም መለገሳችን የሀገር ግዴታችን ነው ብለዋል፡፡

አክለውም ህወሓትን ለመመከት ህዝቡ ከመከላከያ ሰራዊቱ፣ ከክልል ልዩ ኃይሎች እንዲሁም ከሚልሻዎች ጎን በመቆም ደም በመለገስ እና  የተቻለውን ድጋፍ በማድረግ ሀገራዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት ከራሱ አልፎ የውጭ ወራሪዎችን ምኞት ለማሳካት ሲል ህፃናትን ለጦርነት በማሰለፍና እያሰራጨ የሚገኘውን ሀሰተኛ መረጃ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያወግዘው ይገባል ነው ያሉት፡፡

በመርሐ-ግብሩ የተሳተፉ አርቲስቶች በበኩላቸው ግንባር ድረስ ተገኝተው ሠራዊቱን ለማነቃቃት ፈቃደኞች እንደሆኑ ተናግረዋል።

(በአመለወርቅ መኳንንት)