የኦሮሚያ ክልል የአምራች ዘርፍ ንቅናቄ እየተካሄደ ነው

ሚያዝያ 25/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል የአምራች ዘርፍ ንቅናቄ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

“ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል የተጀመረው ሀገር ዐቀፍ የአምራች ዘርፍ ንቅናቄ “ኦሮሚያ ታምርት” በሚል በኦሮሚያ ክልል ለማስጀመር ነው መርኃ ግብሩ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የንቅናቄ መድረኩ በአምራች ዘርፍ የሚስተዋሉ እንቅፋቶች እንዲሁም ስኬቶች ምንድናቸው በሚሉና ሌሎች ጉዳዮች ላይም ትኩረቱን አድርጓል።

የአምራቹ ዘርፍ ኢኮኖሚውን ዘርፍ በመያዝ ድህነትን ለመቀነስ ጉልህ ሚና እንዳለውም ተጠቁሟል።

በዙፋን አምባቸው

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW