የኦሮሞ ባህል ማዕከል ያሰለጠናችውን የአርት አማተሮች እያስመረቀ ነው

ግንቦት 18/2014 (ዋልታ) የኦሮሞ ባህል ማዕከል ለ5ኛ ዙር ለሁለት ወር በተለያዩ የአርት ሙያ ያሰለጠናችውን የአርት አማተሮች በኦሮሞ ባህል ማዕከል እያስመረቀ ይገኛል።

ማዕከሉም “አርት ለዘላቂ ሰላም፣ ለአንድነት፣ ለሀገር ልማት፣ ለሀገር ብልጽግና እና ለሀገር እድገት” በሚል ርዕስ ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ስልጠናውም ለ200 ስልጣኞች የተሰጠ መሆኑን የገለፁት የኦሮሞ ባህል ማዕከል ዳይሬክተር ጌቱ ቢረራ ስልጠናውን ለሁለት ወር መሰጠቱን ጠቁመዋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ አርት ለሀገር እድገት፣ ሰዎችን ለማስተማር፣ የሀገርን ሉዐላዊነት ለማስከበር ጉልህ ድረሻ እንዳለው የተገለፀ ሲሆን የኦሮሞ አርትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱም የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሰኣዳ ኡስማን፣ የኦሮሞ ባህል ማዕከል ዳይሬክተር ጌቱ ቢረራ፣ አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎችን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች ተገኝተዋል።

በእመቤት ንጉሤ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW