የከረዩ አባገዳ በአሸባሪው ሸኔ ተገደሉ

ኅዳር 24/2014 (ዋልታ) የከረዩ አባገዳ ከድር ሀዋስ ቦሩ በአሸባሪው ሸኔ መገደላቸውን የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ገለጸ፡፡

በከረዩ አባገዳ ላይ በአሸባሪው ሸኔ በተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡

ሸኔ በየጊዜው በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጽመው ግድያ አሸባሪው ቡድኑ ሕዝባዊ ዓላማ እንደሌለው ማረጋገጫ መሆኑን የክልሉን ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ዋቢ አድርጎ ኢብኮ ዘግቧል፡፡

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!