የካፊቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓልን ለማክበር ዝግጅት ማጠናቀቁን የካፋ ዞን አስታወቀ

መስከረም 4/2014 (ዋልታ) የካፊቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓልን (ማሽቃሬ ባሮ) ለማክበር ዝግጅት ማጠናቀቁን የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንደሻው ከበደ አስታወቁ፡፡

የማሽቃሬ ባሮ በዓል ከዘመን ዘመን የሚሸጋገርበት እና አዲስ ተስፋ የሚሰነቅበት መሆኑን የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው የዘንድሮው በዓል ከመስከረም 9 ቀን እስከ መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚከበር ገልጸዋል፡፡

አክለውም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ የብሔሩ ተወላጆች እና መላው ኢትዮጵያዊን በዚህ በብሔሩ ዘንድ ትልቅ ቦታ በሚሰጠው በዓል ላይ እንዲታደሙ እና ለምለሚቱን ካፋ እንዲጎበኙ ጥሪ ማስተላለፋቸውን የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን የላከልን መረጃ ያሳያል፡፡