የክልል መንግሥታት በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

የካቲት 25/2014 (ዋልታ) የክልል መንግሥታት 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።
የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በማረፋቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
በተመሳሳይም የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ በአቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ሀዘን በክልሉ ሕዝብና መንግሥት ስም ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በቅዱስነታቸው ዕረፍት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው ለመላው የእምነቱ ተከታዮች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡