የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤ የመከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ወሰኑ

ሐምሌ 16/2013 (ዋልታ) – የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤ  ጌጢቱ ሲሳይ የመከላከያ ሠራዊትን  ለመቀላቀል መወሰናቸው ተገለጸ፡፡

አፈ-ጉባኤዋ ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ ላባደር ክፍለ ጦር ኮምቦልቻ ብርጌድ ከተራ ተዋጊ እስከ ውጊያ ኦፕሬተር፣ እንዲሁም እስከ 1992ዓ.ም የሀገር መከላከያ ሰራዊት  ውስጥ  በተለያዩ ስራዎች የስራ ድርሻዎች አገልግለዋል፡፡

ከኮልፌ ክ/ከተማ ኮሚዪኑኬሽን ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በነገው እለት ወደ ውጊያ ግንባር ጉዞ ለማድረግ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተናግረዋል፡፡

«ጁንታው እኛ እያለን ሀገር ለማፈራርስ ማሰቡ ትክክል ባለመሆኑና ልጆቼን ማሳደግ የምችለው ሀገር ሰላም ስትሆን በመሆኑ የሀገርን ጥሪ ተቀብያለሁ›› ያሉት አፈ-ጉባኤዋ ‹‹የሀገር ጥሪን ስቀበል ለመጪው ትውልድ ፍቅርን አስተምራለሁ›› ብለዋል፡፡

ለሀገራችን አንድነት ሁላችንም የተቀጣጠለውን የመከፋፈል እሳት ማጥፋት አለብን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የፅህፈት ቤቱ ባለሞያዎች የሀገሪቱንን ጥሪ ተቀብለው ወደ ውጊያ ግንባር ስለሚሄዱ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በመስጠት ሽኝት አድርገውላቸዋል፡፡