የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአሸባሪው ሕወሓት መዘረፉ ተገለፀ

ኅዳር 30/2014 (ዋልታ) የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአሸባሪው ሕወሓት መዘረፉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

ፓርኩ በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ከፍተኛ ዝርፊያ እና ጉዳት እንደደረሰበት ተረጋግጧል፡፡

የሽብር ቡድኑ ከተማውን በወረረበት ጊዜ የሰው ህይወት ማጥፋትን ጨምሮ በተለያዩ የሕዝብና የመንግሥት እንዲሁም የግል ንብረቶች ላይ ዝርፊያና ውድመት መፈፀሙ የታወቀ ሲሆን የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክንም መዝረፉንና ንብረት ማውደሙም ተገልጿል።

ኮርፓሬሽኑ የተፈፀመውን ዝርፊያና ውድመት በማጥናት በአይነትና በገንዘብ የደረሰውን የጉዳት መጠን በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።