የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር በማሻቀብ ላይ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር በማሻቀብ ላይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሰፈሩት የጽኑ ሕሙማን ክፍል ያለውን ዐቅም ሁሉ አሟጦ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

በዚህ ወቅት፣ በፍጹም የጥንቃቄ ርምጃዎችን ቸል ልንል አይገባም።

የራሳችንን ሕይወት እንታደግ፣ የሌሎችንም ሕይወት እናትርፍ! የአፍ እና የአፍንጫ ጭንብሎችን በአግባቡ በመጠቀም የጤና ባለሞያዎቻችንን እናግዝ ሲሉ መልዕክታቸውን አስፍረዋል።