የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሕዝብ ለህልውና ዘመቻው ከ57 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

ነሐሴ 3/2013 (ዋልታ) – በአማራ ክልል ከዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሕዝብ ለህልውና ዘመቻው ከ57 ሚሊዮን ብር በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቡን የአስተዳደሩ ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታወቀ።

የአስተዳደሩ የመንግሥት ሠራተኞች ቀድም ሲል 20 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ወስነዋል።

የኮሚቴው አስተባባሪ ወይዘሮ ዝና ጌታቸው ለኢዜአ እንደገለጹት የአስተዳደሩ ሕዝብ አሸባሪው የህወሃት ቡድን የከፈተውን ጦርነት ለመመከት ድጋፉን አድርጓል።

ከድጋፉ ውስጥም 31 ሚሊዮን ብር የሚሆነው ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከአርሶ አደሮችና ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እንደተሰበሰበ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም 21 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ 500 ኩንታል ጥራጥሬና 250 ፍየሎች ድጋፍ ወደ ግንባር መላኩን ገልጸዋል።

ሕዝቡ በዘመቻው ለሚሳተፉት የአገር መከላከያ ሠራዊት፣የአማራ ልዩ ሃይልናና ሚሊሺያ የሚያደርገውን ድጋፍ መቀጠሉንም ተናግረዋል።