የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የደስታ መግለጫ አስተላለፈ

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት

ግንቦት 8/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሆነው ድጋሚ በመመረጣቸው የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፈ።

የሶማሊያ ፓርላማ ሀሰን ሼክ ሞሀመድን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አድርጎ መምረጡ ይታወቃል።

ትናንት በተካሄደው ምርጫ የመጨረሻ ድምፅ አሰጣጥ ሞሀመድ ስልጣን ላይ የነበሩትን መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆን በማሸነፍ ነው የተመረጡት።

በ3ኛው ዙር 328 ድምፅ ያለው የሶማሊያ ፓርላማ ባደረገው ምርጫ ሀሰን ሼክ መሃመድ በስልጣን ላይ ያሉትን መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆን ከአጠቃላይ ድምፅ የ214ቱን በማግኘት ነው ለማሸነፍ የቻሉት።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW