የዓድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል

የካቲት 22/2014 (ዋልታ) የካቲት 23 ቀን 2014 ዓ.ም የሚከበረውን የዓድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ በእለቱ ከማለዳው 12፡00 ሰዓት 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር ማሳወቁን የኢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

126ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ቀን በነገው ዕለት በመላ አገሪቱ ይከበራል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW