የዘንድሮው የቶታል ኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ለዓለም የሚያሳይበት መሆኑ ተገለፀ

ጥር 13/2014 (ዋልታ) የዘንድሮው የቶታል ኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ለዓለም የሚያሳይበት መሆኑ ተገለፀ።

21ኛው የቶታል ኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል።

በአገሪቱ ባለው ወቅታዊ ችግር ምክንያት የተራዘመው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ የሚከናወን ሲሆን የዘንድሮው ውድድር “መፀዳዳት በሽንት ቤት” የሚል መሪ ቃልን አንግቦ ይከናወናል።

በ21ኛው የቶታል ታላቁ ሩጫ 25 ሺሕ ሰዎች የሚሳተፋበት ሲሆን ከታዋቂ አትሌቶች በወንዶች አቤ ጋሻው በሴቶች የዓለምዘርፍ የኋላን ጨምሮ በርካታ አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሏል።

በተጋባዥነት ደግሞ የዩጋንዳ እና የኬኒያ አትሌቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ አዘጋጆች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።