የዘይት እጥረትን ለመፍታት ከባለሃብቶች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው

ለበርካታ ጊዜያት ለማህበረሰቡ ችግር ሆኖ የዘለቀውን የዘይት እጥረት ለመፍታት ከባለሃብቶች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የዘይት እጥረትን ለመፍታት እንዲሁም የዋጋ ንረትን ለመቀነስ የሀገር ውስጥ አምራቾች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እስኪገቡ ምርቶቹ ከቀረጥ ነፃ የሚገቡበት መንገድ መመቻቸት እንዳለበት በመድረኩ ተገልጿል::

እየተስተዋለ ያለውን የዋጋ ንረት ለማስተካከል ህገ ወጥ ንግድን ለማስቀረት መሰራት እንዳለበትም ተመላክቷል::

በአሁኑ ወቅት ዘርፉን ለማጠናከር እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ቢሆንም ዘርፉ ካለበት ችግር አኳያ ተመጣጣኝ ስራዎች አለመሰራታቸው ተገልጿል::

ለችግሩም ዘላቂ መፍትሄን ለማምጣት በዘርፉ የተሰማሩ አካላትን አቅም ማጎልበት እንዲሁም የማምረት አቅምን መጨመር በዘርፉ የሚታዩ እክሎችን ለመፍታት በር ከፋች እንደሆነም ተጠቁሟል::

በዘይት ምርት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍም የዋጋ ማረጋጋት ተግባር ቀዳሚ ስራ ሊሆን እንደሚገባም ተገልጿል፡፡

(በሄብሮን ዋልታው)