የዚምባቡዌ እና የሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ

ጥር 23/2014 (ዋልታ) በ40ኛው የአፍሪካ ኅብረት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የዚምባቡዌ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍሬደሪክ ሙሲዋ ሻቫ እና የሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤዲቴ ራሞሳ ዳ ኮስታ ቴን ጁአ አዲስ አበባ ገቡ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ጀኔራል ዳይሬክተር ፈይሰል አልይ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

40ኛው የአፍሪካ ኅብረት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ የፊታችን ረቡዕ እና ሐሙስ ይካሄዳል።