የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት አምባሳደር የተማሪዎች የሽልማት ሥነሥርዓት አካሄደ

ሰኔ 12/2013 (ዋልታ) – የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ጊዜ የፕሬዝዳንት አምባሳደር የተማሪዎች የሽልማት ሥነሥርዓት አካሂዷል።

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደቱን ጤናማ ከማድረግ ባለፈ 3 ነጥብ 75 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲው አምባሳደር አድርጎ መሾሙን አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ ይህ ዘመን የዕውቀትና የምርምር እንጂ የመሳሪያና የጸብ አለመሆኑን ገልፀው፣ ተማሪዎች በወጣትነት እድሜያቸው መልካም ስራን ለሀገራቸው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ዜጎችን ብቁ አድርጎ ተተኪ ሀይልን በማፍራት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

የመማር ማስተማር ሂደቱ በተሳካ መልኩ እንዲከናወን ተማሪዎች የመጡበትን አላማ አንግበው ማስቀጠል ሲችሉ መሆኑ ተጠቁሟል።

በሥነሥርዓቱ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የፕሬዝዳንትነት አምባሳደር ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።

(በሀኒ አበበ)