ታኅሣሥ 14/2014 (ዋልታ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና የድሬዳዋ ፖሊስ ግንባር ላይ እየተፋለመ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለውን ድጋፍ አደረጉ።
የፌደራል ፖሊስ ሰራዊት ከመንግሥትና ከሕዝብ የተሰጠውን አደራ በመቀበል የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ ለመግታት በኦሮሚያ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ በመተከል፣ በካማሺ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ተናግረዋል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር በበኩላቸው እኛ እያለን አገር አትደፈርም ብሎ ለውድ ህይወቱ ሳይሰስት በጀግንነት በመታገል የሽብር ቡድኖቹ ሽንፈት እንዲከናነቡ ላደረገው ሠራዊት ትልቅ ክብር ይገባል ብለዋል።
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽነር አለሙ መግራ እንደገለጹት አገርን በጀግንነት መጠበቅና ሕዝብን በሰብዓዊነት ማገልገል ትልቅ ክብርና እድለኝነት ነው።
በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሀር የተመራው ልዑክ 45 ሰንጋዎችን፣ የምግብ እቃዎች፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ የድሬዳዋ ፖሊስና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በግዳጅ ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላትንም በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል ተገኝተው ማበረታታቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለሆናችሁ ደስተኞች ነን!