የጀግንነት ቀን መልዕክት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጳጉሜ 4/2013 (ዋልታ) አገር የምትጎዳው ጀግኖች በጎደሉበት መስክ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

‹‹ጀግንነት የታጋይነት፣ የጽናትና የአሸናፊነት  ውጤት ነው›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  ጀግንነት መልከ ብዙ ስለመሆኑ አንስተዋል።

ስለጀግንነት ቀን ባስተላለፉት መልዕክትም ‹‹የጦር፣ የግብርና ፣ የሳይንስ፣ የንግድ፣ የዕውቀት፣ የኪነ ጥበብ፣ የመንግሥት ሥራ፣ የአገልግሎት ሰጪ፣ ጀግኖች አሉ አንዱ ጀግንነት ያለ ሌላው አይኖርም›› ብለዋል።

አገር በራሷ ቆማ፣ ራሷን ችላ፣ የራሷን ዕድል እንድትወስን ሁሉም ዓይነት ጀግኖች ያስፈልጓታል ያሉም ሲሆን፤ አገር የምትጎዳው ጀግኖች በጎደሉበት መስክ ነው ሲሉ ስለጀግንነት አስፈላጊነት ገልፀዋል፡፡