የጂግጂጋ ከተማ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

ጥቅምት 28/2014 (ዋልታ) አሸባሪውን ሕወሓትና አጋሮቹን የሚያወግዝ ትዕይንተ ሕዝብ በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ ተካሄደ።
በሰላማዊ ሰልፉ ከ20ም ቀበሌ የተውጣጡ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።
ነዋሪዎቹ አሸባሪውንና አገር አፍራሹን የሕወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት መንግሥት የሚያደርገውን የኅልውና ዘመቻ እንደሚደግፉ ገልፀው ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጎን እንደሆኑ ተናግረዋል።
በሰልፉ የአሸባሪውን ቡድንና አጋሮቹን እኩይ ድርጊት የሚያሚያወግዙ የተለያዩ መፈክሮች መስተጋባታቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።