የገበያ አሻጥር በሚፈጽሙ አምራቾች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

ጥቅምት 17/2015 (ዋልታ) ምርት መደበቅን ጨምሮ የገበያ አሻጥር በሚፈጽሙ አምራቾች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ገለጹ።

ከከተማ እና መሰረተልማት ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ዱከም የሴራሚክ ፋብሪካን መጎብኘታቸውን የጠቀሱት ሚኒስትርሩ፤ በርካታ ምርት ለገበያ ሳይቀርብ ተከማችቶ መመልከታቸውን ገልጸዋል።

የፋብሪካው ኃላፊዎች በአፋጣኝ ወደ ሕግ እንዲቀርቡ መደረጉን ገልጸው፤ እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።