ሐምሌ 07/2013 (ዋልታ) – የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ጉምሩክ ኮሚሽንና ብሄራዊ ሎተሪ በአዲስ አበባ የ100 አቅመ ደካሞችን ቤቶች አድሳት አስጀመሩ።
የቤቶቹን አድሳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በየካ ክፍለ ከተማ በመገኘት አስጀምረዋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ጉምሩክ ኮሚሽንና ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር በጋራ በመሆን በክረምቱ 100 የአቅመ ደካሞችን ቤቶች በማደስ ለነዋሪዎቹ ለማስረከብ ስራው ዛሬ ተጀምሯል።
መርሃ ግበሩን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተቋማቱ ላደረጉት ተነሳሽነትና በጎ ተግባር አመስግነዋል።
በለውጡ ሂደት የበጎ ፈቃድ አገልገሎት እየተለመደና ባህል እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው ይሄው ተጠናክሮ መቀጠል የኖርበታል ብለዋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ጉምሩክ ኮሚሽንና ብሄራዊ ሎተሪ ለቤቶቹ እድሳት በጋራ ያዋጡትን 10 ሚሊዮን ብር ምክትል ከንቲባዋ ተረክበዋል።
በመርሃ ግበሩ ማስጀመሪያ ላይ የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌውን ጨምሮ የተቋማቱና የአስተዳደሩ ሰራተኞች እንዲሁም ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በዘንደሮው ክረምት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2 ሺህ አቅመ ደካሞችንና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች መኖሪያ ቤቶች ለማደስ መታቀዱን ኢዜአ ዘግቧል።