የጉለሌ ክፍለ ከተማ 151 ፕሮጀክቶችን አስመረቀ

ግንቦት 06/2013 (ዋልታ) – በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክፍለ ከተማ ከ320 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያስገነባቸውን 151 ፕሮጀክቶች አስመረቀ።

በክፍለ ከተማው ከ2011 እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ 118 ፕሮጀክቶች ለመገንባት ታቅዶ የነበረ ሲሆን 151 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸው ተገልጿል፡፡

በትምህርት ዘርፍ 57 ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለማህበረሰቡ ለአገልግሎት የበቁ ሲሆን የስራ እድል ፈጠራ 49 ፕሮጀክቶች፣ በወጣት ስብዕና መገንቢያና ስፖርት ማዘውተሪያ 7 ፕሮጀክቶች፣ በጤናው ዘርፍ 14 ፕሮጀክቶች እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ በቢሮ ግንባታና ማስፋፊያ 24 ፕሮጀክቶች ለምረቃ መብቃታቸው ተጠቅሷል።

በምረቃ ስነስርዓቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ጃንጥራር አባይና ሌሎች የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

(በምንይሉ ደስይበለው)