የጎልማሶች ትምህርትን ለመደገፍ የሚያስችል የዘርፉ ባለሙያዎች ማኅበር ተመሰረተ

የካቲት 22/2014 (ዋልታ) የጎልማሶች ትምህርትን በሚጠበቀው ደረጃ ውጤታማ ለማድረግ እና ለመደገፍ የሚያስችል የዘርፉ ባለሙያዎች ማኅበር መመስረቱ ተገለጸ፡፡

ዘርፉን አሁን ካለበት ችግር ለማላቀቅ ያለመ የዘርፉ ባለሙያዎች ማኅበር በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት የመመስረቻ ጉባዔ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩም የጎልማሶችና የሕይወት-ዘመን ትምህርት እና ማኅበረሰብ ልማት (ጎሕትማል) ባለሙያዎች ማኅበር በኢትዮጵያ በሚል ስያሜ ማህበሩ ተመስርቷል፡፡

የሙያ ማኅበሩ መመስረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን የሙያ ማኅበሩን በቀጣይ የሚመሩ አመራሮችም ምርጫ ተካሂዷል፡፡

በምስረታ ጉባኤው ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ የተማረ የሰው ኃይል ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW