የጣልያን አምባሳደር አጎስቲን ፓሌሴ የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለመስጠት ተስማምተዋል

የካቲት 11/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር አጎስቲን ፓሌሴ በአሶሳ የዕምነበረድ ፓርክ ግንባታ የሚውል የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለመስጠት መስማማታቸውን የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ ገልጸዋል፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለጹት ድጋፉን ለማድረግ ከስምምነት የተደረሰው ከዚህ ቀደም በተገባው ቃል መሰረት መሆኑን ጠቁመው ድጋፉ በአሶሳ ለሚገነባው የዕምነበረድ ፓርክ እንዲሁም የአሶሳ የዕምነበረድ ማሰልጠኛን ለመደገፍ የሚውል ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ የዕምነበረድ ሙያ ሰልጣኞች ወደ ጣልያን በመሄድ ስልጠና የሚያገኙ ሲሆን የተማረ የሰው ኃይላችንን ለማሳደግ የምንሰራው ስራም በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል፡፡