የካቲት 15/2014 (ዋልታ) ፀሐይ ሪል ስቴት እያስገነባቸው ያሉ የንግድ ማዕከል እና የአፓርትመንት ህንፃ ግንባታ በፍጥነት እየተከናወኑ መሆናቸው ተገለፀ።
ተቋሙ አዲስ እያስገነባ ስላለው የገበያ ማዕከልና የአፓርትመንት ህንፃ ግንባታ ዛሬ ለሚመለከታቸው አካላት ገለፃ አድርጓል፡፡
በዚህም ግንባታው በ2013 ዓ.ም የተጀመረው የንግድ ማዕከል 6ዐ በመቶ እንደተጠናቀቀ የገለጸው ተቋሙ የአፓርትመንት ህንፃ ግንባታው 40 በመቶ መድረሱን አስታውቋል።
በ2015 ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የገበያ ማዕከል ለ900 ዜጎች የሥራ እድል እንደፈጠረም ተጠቁሟል።
የገበያ ማዕከሉ ሲጠናቀቅ በርካታ አገልግሎቶች ይሰጣልም ተብሏል።
በሱራፌል መንግስቴ