የፌደራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ድንጋጌዎች ማብራሪያ ሰነድ ተዘጋጀ

ሐምሌ 15/2013 (ዋልታ) – የፌደራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ድንጋጌዎች ማብራሪያ ሰነድ መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡

የፌደራል የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 የፌደራል አስተዳደር ሥነ-ስርዓት አዋጅ ድንጋጌዎችን ይዘት ለማብራራት ያለመ ሰነድ ነው፡፡

የሰነዱ ማብሰሪያ ላይ የተገኙት የፌደራል ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተስፋዬ ዳባ ባለፋት ሶስት ዓመታት የፍትህ ዘርፍ ሪፎርሞችን ለማገዝ የህግ ማሻሻያዎች ሲካሄዱ እንደነበር አንስተዋል፡፡

ባለፈዉ ዓመት እንዲፀድቅ የተደረገዉ አዋጅ የመንግስት ተቋማት አስተዳደር አሰራሮችን ለህዝብ ግልጽ እንዲሆን ለማስቻል የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

ሰነዱ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በጂ.አይ.ዜድ የገንዘብ ድጋፍ እንዲዘጋጅ የተደረገ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ ድንጋጌዎቹን በማዘጋጀት ሂደት ለተሳተፉ አካለት ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡

(በሰለሞን በየነ)