ሐምሌ 11/2013 (ዋልታ) – የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና የፖሊስ አባላት እንጦጦ ችግኝ በመትከል በሀገር አቀፋ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተሳተፋ።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ እንዳስታወቁት የፌደራል ፖሊስ የሀገር ሰላም እና የአካባቢን ፀጥታ ከመጠበቅ ባሻገር በተለያዩ የልማት ስራዎች በመሳተፍ የተጣለበትን ማህበራዊ ኃላፊነት በመወጣት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
“ኑ ኢትዮጵያን እናልብስ “በሚለውን የአረንጓዴ አሻራ ሀገራዊ ጥሪን በመቀበል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ችግኝ በመትከል ላይ እንገኛለን ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፕሬስ ሰክሪታሪያት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።