የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ከዓለም ባንክ ተወካይ ጋር ተወያዩ

ግንቦት 1/2014 (ዋልታ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን እና ምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና የዓለም ባንክ ተወካይ ኡስማን ዲዎን (ዶ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድንን ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም ለልዑካን ቡድኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስልጣንና ኃላፊነትን በተመለከተ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን ልማት ለመደገፍ እያደረገ ያለውን ጥረት ያደነቁት አፈ ጉባኤው ባንኩ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያለቸውን እምነት ገልጸዋል።
የዓለም ባንክ ተወካዩ ኡስማን ዲዎን በበኩላቸው ምክር ቤቱ እያከናወነ ያለውን ሥራ በማድነቅ በቀጣይም የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለመደገፍ እና አብሮ ለመስራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ዓለም ባንክ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በቅደም ተከተል የሚከናወኑ ተግባራትን ለመለየትና ለማቀድ የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሥራዎች እንዲሰሩና የዓለም ባንክ ድጋፍም ከፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደማይለይ መግለጻቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በማስመልከት ምስጋናቸውንም አቅርበዋል፡፡