የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ የዴሞክራሲ ሰባኪዎች ለአሸባሪው ሕወሓት ሲወግኑ ማዬት አሳፋሪ ነው አሉ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) “አንዳንዶች ለአሸባሪ ደርጅቱ ሕወሓት ሲወግኑ ማዬት አሳፋሪ ነው” ሲሉ የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያን ተስፋ ለማጥፋት ሌት ተቀን እየሰሩ መኖርም አስገራሚ መሆኑን አክለዋል።

ዴሞክራሲን የሚሰብኩ አገራት ጨቋኝና አሸባሪ ድርጅቶችን በመደገፍ ሰብኣዊ መብትን በመጣስ መከራውን ሲያራዝሙ ማዬት አስደንጋጭ ነው ብለዋል፡፡

“እናንተ ዴሞክራሲንና ሰብኣዊ መብትን ትሰብካችሁ መልሳችሁ ግን በኢትዮጵያ ላይ ቁጥር አንድ ጨቋኝና ስቃይ ፈጣሪ የሆነን አካል ትደግፋላችሁ” ሲሉ ነው ተቃውሟቸውን በቲውተር ገጻቸው የገለፁት።

ሚኒስትሯ በቲውተር ገጻቸው ሰብኣዊ እርዳታ ለጋሽ ነን ባይ አንዳንድ ድርጅቶች ሰብኣዊ መብት እየጣሱ መሆኑንም አስፍረዋል፡፡