የፕሬዝዳንት ፑቲን ለጠ/ሚ ዐቢይ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

መስከረም 28/2014 (ዋልታ) የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቪላደሚር ፑቲን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።
ፕሬዝዳንቱ የመልካም ምኞት መልእክታቸውን ያስተላለፉት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሚ መሾማቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ፕሬዝዳንቱ በቴሌግራም በላኩት መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በቀጣይ የሥራ ዘመናቸው የሁለቱ አገራት ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነትን ለማጎልበት ብሎም ለአፍሪካ ጸጥታ እና መረጋጋት በይበልጥ እንደሚሰሩ እምነቴ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን በመልዕክታቸው የኢትዮጵያና የሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነት በመልካም ወዳጅነትና በመከባበር ላይ የተመሠረተ እንደሆነ መግለፃቸውን በኢትዮጵያ ከሩሲያ ኢምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት እ.አ.አ 1943 ዓ.ም መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!