ሚያዝያ 18/ 2014 (ዋልታ) የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ አመሠራረት እና ሂደት ላይ፣ ከኮሚሽነሮቹ እና ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ይገኛሉ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሠ ጫፎ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በቀረበ ጥያቄ መሠረት የውይይት መድረኩ እንደተዘጋጀ ጠቁመዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ ራሄል ባፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሀገራዊ ምክክሩ ተስፋ የተጣለበትና ለሀገራችን ብቸኛ አማራጭ በመሆኑ ቀጣይ በሚኖረው ሂደት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የኮሚሽነሮቹን የአሰያየም ሂደት በተመለከተ በአፈ ጉባኤ ታገሰ እና በፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር ) ማብራሪያ መሰጠቱን የምክር ቤቱ መረጃ ጠቁሟል።