የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲ እንደሚሰጥ ተገለፀ

ሰኔ 22/2014 (ዋልታ) የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ በሆሳዕና ፣ በወራቤና በወልቂጤ ከተሞች የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃና ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅት የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በትምህርት ቤቶች ሳይሆን በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በኤሌክትሮኒክስ /online/ መስጠት እስከሚጀመር ድረስ በዩኒቨርስቲዎች መሰጠቱ ይቀጥላል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲእንደሚሰጥ ተገለፀነው የፈተና ስርቆትና ማጭበርበርን ለማስቀረት ታስቦ በመሆኑ ተማሪዎች ትምህርት፣ በስራና በታታሪነት የሚገኝ መሆኑን አውቀው በርትተው መማርና ማጥናት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትን ጥራትን ለማሻሻል በአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፎች ሌሎችንም የተለያዩ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ መሆኑንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ሦስቱንም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የጎበኙ ሲሆን የ4ኛው አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ማስጀመራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል፡፡