ዩኒቨርሲቲው ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለአትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ ነው

ነሐሴ 19/2014 (ዋልታ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ የክብር ዶክተሬቱን የሚሰጣቸው በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትን እና ያስተማሩትን በተግባር በመኖራቸው እና ሰውን በሰውነቱ ብቻ በማክበራቸው እንደሆነ አመልክቷል።

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ደግሞ ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪካን በስፖርቱ ዓለም በማስጠራት ጀምራ ለኅብረሰተብ ፍቅር እና አንድነት መጎልበት እየተጋች በመሆኑ የክብር ዶክትሬትቱን ሊሰጣት እንደሆነ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!