‘‘ያሬድ ትምህርት ቤት ሊፈርስ ነው’’ በሚል የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም የተሳሳተ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ

ያሬድ ትምህርት ቤት

መጋቢት 25/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ‘‘ያሬድ ትምህርት ቤት ሊፈርስ ነው’’ በሚል የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም የተሳሳተ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ አንዳንድ ወገኖች የተሳሳቱ መረጃዎችን በተደጋጋሚ በመልቀቅ ኅብረተሰቡን ወደ ውዥንብር ለመክተት ጥረት እያደረጉ ይገኛል ብሏል፡፡

በዚህ ሰሞን ‘‘አንጋፋው የሙዚቃ ትምህርት ተቋም የሆነው ያሬድ ትምህርት ቤት ሊፈርስ ነው’’ የሚል መረጃ በማሰራጨት በሕዝቡ ውስጥ ውዥንብር ለመፍጠር የሞከሩ መሆኑን ያስታወቀው ከተማ አስተዳደሩ ነገር ግን በአስተዳደሩም በኩል ይሁን በትምህርት ቤቱ በኩል ምንም የተለየ ነገር የሌለና ይህ መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በዚህም ኅብረተሰቡ እንደዚህ በተደጋጋሚ የሃሰት የበሬ ወለደ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላትን በማጋለጥ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪውን ማስተላለፉን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW