ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያን ለመጉዳት ከግዛቴ የሚነሳ እንቅስቃሴ አይኖርም አለች

ታኅሣሥ 3/2014 (ዋልታ) ከደቡብ ሱዳን በኩል የሚመጣና ኢትዮጵያን ለመጉዳት ያለመ እንቅስቃሴ አሁንም ሆነ ወደፊት እንደማኖር የደቡብ የሱዳንን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪያክ ማቻር (ዶ/ር) አረጋገጡ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል መህዲ ጋር በሁለቱ አገራት በጋራ ጉዳዮች ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚጠቁመው ለኢትዮጵያ ሰላም መስፈን አገራቸው ቁርጠኛ አቋም እንዳላት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።

አምባሳደር ነቢል መህዲ በበኩላቸው ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አስረድተው አንዳንድ የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን ሀሰተኛ ዘገባዎች በማሰራጨት የአገሪቱንና የአመራሩን ገጽታ ለማጠልሸት እየሰሩ እንደሆነም አስታውሰዋል።