ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

ሰኔ 22/2013 (ዋልታ) – ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለ13ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡

ዩኒቨርስቲው በ9 የትምህርት ኮሌጆች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ ከሚያስመርቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 40 በመቶ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ዩኒቨርስቲው ዛሬ የሚያስመርቀው የዛሬ ተመራቂዎችን ጨምሮ ከ26 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ ማስመረቁን የአሚኮ ዘገባ ያመለክታል፡፡