ዲያስፖራው ግለሰብ ለሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል አባላት የ10 በሬዎች ድጋፍ አደረጉ

ታኅሣሥ 29/2014 (ዋልታ) በካናዳ ነዋሪ የሆኑት አገሩ አበራ ለሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል የሰራዊት አባላት የ10 ሰንጋ በሬዎች ድጋፍ አደረጉ።

በሕግ ማስከበር ዘመቻው ጉዳት የደረሰባቸውን የሰራዊት አባላት ከጠየቁ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት “እናንተ የአገር ዘቦች ለእናት አገራችን ክብር ለከፈላችሁት ታላቅ መስዋትነት ከልብ እናመሰግናለን” ብለዋል።

ሁሌም ከጎናችሁ ነን በማለትም ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል 1ኛ ደረጃ ሆስፒታል ኃላፊ ኮሎኔል ሙሉጌታ ተፈራ ዲያስፖራው ለአገሩ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪ የመንግሥትን ጥሪ በመቀበልና ወደ አገር ቤት በመምጣት በኅልውና ማስከበር ዘመቻው ላይ የተጎዱ የሰራዊት አባላትን በመጠየቅ እና በማበረታታት ለተደረገው ድጋፍ ማመስገናቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ አመልክቷል።