ዲያስፖራዎች የተሳተፉበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

ታኅሣሥ 24/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የወደ ሀገር ቤት ጥሪን ተቀብለው ለመጡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጅ ዲያስፖራዎች የተዘጋጀ ማስ ስፖርት ተካሄደ፡፡
በአካል ብቃት እንቅስቃሴው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ ዲያስፖራዎች በመዲናዋ ቆይታቸው ኢትዮጵያዊነትን፣ አንድነትን፣ መዋደድንና መረዳዳትን የሚያጠናክሩባቸው የተለያዩ ሁነቶች መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ብርሀም ታደሰ በበኩላቸው “ስለሀገራችሁ ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ የሞገታችሁ፣ ከፊት የቆማችሁና እውነታውን በማሳየት ኢትዮጵያን አሸናፊ ያደረጋችሁ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ናችሁ” ሲሉ አመስግነዋል። በከተማዋ ቆይታቸው በሌዩ ልዩ ተግባራት ተሳትፏቸው እንዲቀጥል መጠየቃቸውንም የቢሮው መረጃ ይጠቁማል።
ዲያስፖራዎቹ የከተማዋን ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሚጎበቹበት መርሃ ግብርም መዘጋጀቱ ነው የተገለፀው።